አገራችን የጀመረችውን ከድህነት አዙሪት የመውጣት ትግሉን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የልማት፣ የሠላም፣ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ስትራቴጂዎች ተነድፈው በመተግበር ላይ ናቸው፡፡ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ጀምረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣንና ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች መሻሻል ተስፋ ሰጭና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ቢሆኑም የአገራችን ማህበራዊ ችግር ውስብስብና ለረዢም ጊዜ ስር የሰደዱ በመሆናቸው በቀላሉ የሚቀረፍ አይደሉም፡፡ እነዚህን ድህነትና የመልካም አስተዳደር እጦት የወለዳቸውን ማህበራዊ ችግሮች ማስወገድ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ራዕያችን እውን ለማድረግ በየዘርፉ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ማህበራዊ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በማቃለል ማህበራዊ ፍትህ የማንገስ ህዝባዊ ተልዕኮ ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው፡፡ የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች የህብረተሰቡን መልካም አኗኗር የሚጐዱና ምርታማነትን የሚቀንሱና የአገሪቱን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን የሚጐዱ በመሆናቸው ችግሮቹን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር ብሎም ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት ለአንድ የመንግስት መስሪያቤት ብቻ የሚተው ጉዳይ አይሆንም፡፡ በመሆኑም የመላው ሕብረተሰብ፣ የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን የተቀናጀ፣ የተቀነባበረና የተናበበ ጥረት የሚጠይቅ ይሆናል፡፡

የሠራተኛናማህበራዊ ጉዳይ 1949 . በአዋጅ ተቋቁሞ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ተጠሪ /ቤት ዘርግቶ ይንቀሳቀስ እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ይህ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መስሪያ ቤት በየግዜውየተለያዩ ስያሜዎችነበሩት፡፡ቢሆንም በሥራ እንቅስቃሴና የሚያተኩርባቸዉ ተግባራት በቅርጽ ቢለያዩም በይዘት ተመሳሳይነት እንዳላቸዉ መረዳት ይቻላል፡፡በኢትዮጽያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ክልሎች የራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደተረጋገጠ 1985 . ጀምሮ በክልላችን ከተቋቋሙት አስፈፃሚ ቢሮዎች መካከል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነዉ::

ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስያሜዉ እንደሚያመለክተዉ የአሠሪና ሠራተኛን ጉዳይና የማህበራዊ ጉዳይን የትኩረት ዘርፎችን ያቀፈ ሲሆን በነዚህ ዘርፎች በርካታ ተግባራትን ያከናወነና በማከናወን ላይ ያለ ቢሮ ነው፡

 

 

 
Customer Sats.Study
Announcement
We have 2 guests online
  • Photo Title 1
  • Photo Title 2
  • Photo Title 3
  • Photo Title 4
  • Photo Title 5
  • Photo Title 6
  • Photo Title 7
  • Photo Title 8
  • Photo Title 9